ይድረስ ለአባ ፍቅረስላሴ ፀጋው ተረፈ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅድስት ማርያም ወ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

12/02/2014 22:22
Page 1 of 2
 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅድስት ማርያም ወ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
ከ ለሰላም ለአንድነትና ለሕግ የበላይነት የተቋቋመ መድረክ
ለ መላው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመናን የቀረበ የሕብረት ጥሪ
 
September 22 2013
 
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለዓመታት ሲንከባለል የቆየውን ብልሹና ሥርዓት ያጣ አሠራር ሥርዓት ለማስያዝ ሲባል በተለያየ ጊዜ ምዕመናን በግል ለቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ምክር ሲለግሱ ቢቆዩም ዶሮ ጥሬዋን እንዲሉ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ ሲያልፈው ቆይቷል።
እንደዚሁም ይሠራል ተብሎ ለታቀደው ካቴድራል ሥራ እንዲያግዝ በ November 2010 በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የተቋቋመው አማካሪ ኮሚቴ በታዘዘው መሠረት ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ተግባራዊነትና ድጋፍ ሲያፈለላግ የተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን አነጋግሯል። የተጠየቀውን ድጋፍ ከመስጠታቸው በፊት፣ መሥሪያቤቶቹ ቤተ ክርስቲያናችን እንድታሟላ የጠየቁትን Business Plan፣ የቤተ ክርስቲያን የመተዳደሪያ ደንብ እና ኦዲት የተደረገ የቤተ ክርስቲያኗ የገንዘብ ሪፖርት እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል። መሥሪያ ቤቶቹ የጠየቁትን ለማቅረብ ባለመቻሉ የአማካሪ ኮሚቴው ለቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪና ለቦርዱ ሊቀ መንበር ጥያቄውን አስተላልፏል። አስተዳደሩ የተጠየቀውን ለማቀረብ ባለመቻሉ እስከዚያን ድረስ በቤተ ክርስቲያኑ ተሸፋፍኖ የቆየው ችግር ብቅ ማለት ጀመረ።
የተጠየቀውም ሪፖርት ሊቀርብ እንደማይችል በግልጽ ተነገረ። የተሰጠውም ሰበብ “ እኛ በቃለ አዋዲ ነው እምንተዳደረው” የሚል ነበር። ይኸው እውነታ ካቴድራል ለመሥራት ሳይሆን እቅዱ የካቴድራል ስዕል አሳይቶ ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚደረግ ዘመቻ አስመስሎታል።
የአማካሪ ኮሚቴው በዚህ ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያሰበውን ማሻሻያዎች በዝርዝር ማቅረቡ የሚታወስ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ሰሚ ሲያጣ ሁለተኛውን ሪፖርቱን ዲሰምበር 2012 ላይ ለሕዝብ እንዲደርስ አድርጓል።
ከዚያም በኋላ ችግሩን አሁንም ምዕመኑን በመሰብሰብ አወያይቶ በማስወሰን የሚሻለውን መንገድ መከተል ሲቻል በአባ በኩል የተወሰደው እርምጃ ግን የሚከተለው ነው።
- መቅደስ ላይ አብሮአቸው የሚያገለግለውን ካህን ወንጅሎ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ
- ይህንን ብልሹ አሠራር ለማስተካከል በግልጽ የቀረበላቸውን ሪፖርት የፖለቲካ ይዘት ያለው ማስመሰል
 
Page 2 of 2
 
- ዊኒፔግ ላይ በተለይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገናኘን ሃይማኖታችን እንጂ ዘራችን አለመሆኑ እየታወቀ በዘር ሊከፋፍሉን እርስ በራሳችን ሊያባሉን መሞከር
- ጃንዋሪ 8 2013 በተደረገው ድራማ መሰል ሹም ሽር ላይ ምዕመናንም ሆነ የቀድሞ ኮሚቴ አባላት ሃሳብ ለመስጠት ያደረጉት ሙከራ ውድቅ ማድረግ
- ይባስ ተብሎም ኤፕሪል 14 2013 በተደረገው ስብሰባ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተላለፈለትን ጥሪ አክብሮ ለመጣው ምዕመን አትፈለግም ተብሎ በፖሊስ አንዲባረር ማድረግ
- ወደ ስብሰባው ለመግባት እድል ያገኘውም አስተያየት እንዳይሰጥ ታፍኖ የተሰጠውን መግለጫ ሰምቶ እንዲወጣ ማድረግ
- ሕግና ሥርዓት ይስፈን እያሉ በሚጠይቁት ምዕመናን ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ የስድብ ዘመቻ በማውረድ ዝም ለማሰኘት መሞከር
ይህ በእንዲህ እያለ
- በቅርቡ $65,000.00 በኢትዮጵያ ገዳማትና ጥንታዊ ትምህርት ቤቶች ስም ከቤተ ክርስቲያኗ አካውንት ወጥቶ በአባ ፍቅረ ሥላሴ የግል አካውንት ገቢ መደረጉ ግልጽ ሆነ። ለዚህም ሕገ ወጥ ተግባር እስካሁን የተሰጠ መልስ የለም።
እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ የጠቀስናቸው ሁኔታዎች ሲከሰቱ ብዙ ምዕመናን ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቤተ ክርስቲያንኗን የሰላምና የተቀደሰች የአምልኮ ሥፍራ ሆና እንድትቀጥል ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም ሰሚ አላገኙም።
ይህ በመሆኑ ጉዳዩ ያሳሰበን ምዕመናን በመሰባሰብ “ለሰላም ለአንድነትና ለሕግ የበላይነት የተቋቋመ መድረክ” በሚል ጥላ ሥር ለመሰብሰብና ለመወያየት ተገደናል።
መደረኩ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያናችን አባል ያለምንም ልዩነት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኑን አመራር አካላት ጨምሮ የሚያሳትፍ ጉባዔ በማድረግ ችግሮችን ለመፍታት ሕዝባዊ ጥሪ ያደርጋል።
ዓላማችን ሕግና ሥርዓት ላይ የተመረኮዘ ግልጽ አሠራር ለማስፈን ነው። ይኸው ግልጽ የሆነ አላማችን የምናካሂደው ምዕመኑን ሙሉ በሙሉ በማሳተፍ በምዕመኑ ፍላጎትና ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ብቻ ይሆናል።
በዛሬው ዕለት መድረኩ ሕዝቡ ይጋራቸዋል ብለን የምናምነውን ጉዳዮች ከዚህ ቀጥሎ በተያያዘው መሠረት ለቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሽማግሌዎች በመላክ ጥያቄዎችን አቅርበናል።
ይህም የተጀመረውን ግልጽ የሆነ የሰላምና የውይይት ጥሪ ምዕመኑ እንዲያውቀውና እንዲሳተፍበት ከጎናችን ቆሞ እውነቱን ፈልፍሎ እንዲያወጣ በትህትና ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር። አሜን።