የጥምቀት በዓል

31/01/2014 16:37
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ውሀ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ እንኳን ክርስቲያን፤
ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ ያውቀዋል። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ ይሰብከዋል። የጥንት
ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አበው በሰሩልን ስርአት እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
ካህናት፤ ከዓለም ልዩ በሆነ መንገድ በስብሸባ በዝማሬ፤ አዛውንቱ በይባቤ፤ ሴቱ በዕልልታ፤ ጎልማሶች
በሆታ ሁላችንም ጥምቀት የተሸከመችውን ጥልቅና ምጡቅ ምሥጢር በከፍተኛ ስሜት
እናንጸባርቃታለን። ከጥምቀት ምሥጢር ጋራ የተወሀደውን የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ለባእድ ግልጽ
አድርጎ ለማቅረብና ትውልዱን ለማስተምር ከዚህ ዘመን የከፋ ዘመን ኢትዮጵያን እና ቤተ
ክርስቲያናችንን የሚገጥማቸው አይመስለኝም።ጽድቅ ለመፈጸም ክርስቶስ ተጠመቀ.pdf (430401)